• Dutch
  • English
  • Amharic
የድርጅቱ ተልዕኮ፤ የአተገባበር ሥልት እና የትኩረት አቅጣጫ

ተልዕኮ

ቢለማ ፋውንዴሽን በምስራቅ አፍሪካ አካባቢያዊ ክህሎቶችን የሚያበረታቱና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን በመጀመር በአሁኑ ሰዓት በቀጠናው ያለውን የጤና ክብካቤ አደረጃጀት የበለጠ እንዲሻሻልና እንዲጎለብት በተለይም ነፍሰጡር እናቶችን ተኮር በሆኑ የጤና አደረጃጀቶች ዙሪያ በትብብር የመስራት ፍላጎት ያለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡

የአተገባበር ሥልት

ቢለማ ፋውንዴሽን በክልሉ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ጋር በመተባበር፤ የእናቶች ጤና ክብካቤን ተደራሽነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በተግባር ያስፈጽማል፡፡

የትኩረት አቅጣጫዎች

• በአካባቢው የእናቶች የስነ-ተዋልዶ ጤና ክብካቤን ማሻሻል፤ በተለይም ደግሞ ሚድዋይፎችን በማሰልጠን ረገድ፡፡
• ነፍሰጡር እናቶችን ተኮር የሆኑ የጤና አደረጃጀቶችን ማሻሻልና ማጎልበት፤
• የሰለጠኑ ሚድዋይፎች በትውልድ ቦታቸው ሙያዊ አስተዋፅዖ እንዳያደርጉ እንቅፋት የሆነባቸውን ችግሮች በማስወገድ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመተግበር እገዛ ማድረግ፡፡
• በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ሚድዋይፎችንና ነርሶችን ወደ ማኅጸንና ፅንስ ቀዶ ጥገና ሀኪምነት ማስልጠን የሚቻልበትን ሁኔታ በምርምር የታገዘ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረፅ የእናቶችን የስነ-ተዋልዶ ጤና ክብካቤ ተደራሽነት የሚረጋገጥበትን ሁኔታ ማመቻቸት፡፡