• Dutch
  • English
  • Amharic

መግቢያ

ተቀማጭነቱ በኔዘርላንድ ሀገር የሚገኘው “Bilateral Matters foundation” በአማርኛ “ቢለማ” ፋውንዴሽን የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ከደቡብ ብሔርና ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በክልሉ በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶች ሞት መከላከልን ማዕከል ያደርገ አዲስ ፕሮጀክት ጀመረ፡፡

ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጭው ዓመት 2007 ዓ/ም (2014) ጀምሮ እስከ 2010 ዓ/ም (2017) ከሚተገብራቸው ዓበይት ተግባራት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
   ሀ/  በክልሉ ከሚገኙ የጤና ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በመተባበር የሚድዋይፈሪ ባለሙያ እጥረት በሚታይባቸው ወረዳዎች ለሚገኙ 10ኛ ወይም 12ኛ ክፍል ላጠናቀቁና የክልሉ የጤና ማስልጠኛ ተቋማት የሚያወጡትን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ ዕጩ ሰልጣኞች በመመልመል፡ የሚሰጣቸውን ስልጠና ሲያጠናቅቁ በተመረጡበት ወረዳ ተመድበው የመስራት ፍላጎት ያላቸውን ስልጣኞች የሚድዋይፈሪ ስልጠናን እንዲሰለጥኑ ሙሉ የስልጠና ወጪያቸውን ይሸፍናል፡፡
   ለ/  በክልሉ የእናቶች ጤና አገልግሎትን በተመለከተ ትርጉም ባለው መልኩ ተደራሽነት እንዲኖረው የሚያስችል ለውጥ ለማምጣት ተከታታይ ስራዎችን ይሰራል፡፡

ካላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ዓቢይ ዓላማዎች፤ በፕሮጄክት ደረጃ ተቀርፀው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የሚድዋይፈሪ ስልጠና ፕሮጅክትን በዲፕሎማ ደረጃ ና በቀጣይም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የእናቶች ጤና ክብካቤ መስጫ ተቋማትን ደረጃቸውን የማሳደግ ስራ ፕሮጀክት በተከታይነት የሚተገበሩበትን ሁኔታ ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ይህንንም ለመተግበር ቢለማ ፋዉንዴሽን ከአጋር እህት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሁለቱ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም የሚውል የገቢ ማስባሰብ ስራ በይፋ ጀምሯል፡፡

 

ሚድዋይፎችን ለማሰልጠን የሚያስችል የገንዘብ እርዳታ ከቢለማ ፋውንዴሽን ተገኘ

ቢለማ ፋውንዴሽን በደቡብ ብሔርና ብሔረሰብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የአዋላጅ ነርሶች (ሚድዋይፎች) እጥረት በሚታይባቸው .....

ይቀፕላል....