• Dutch
  • English
  • Amharic
እርዳታዎች

ቢለማ ተቋም የትምህርት ኘሮጀክቶችን የሚረዳና የጤና አጠባበቅ ኘሮጀክቶችን የሚያለማ ነው፡፡

ቢለማ በኢትዮጵያ፣ ናዝሬት ውስጥ ለጊዜው ለትናንሽ ልጆች ብቻ የሆነ የመሠረታዊ ደረጃ ት/ቤት ኘሮጀክት በማልማት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ኘሮጀክት ወደ ተሟላ የመሠረታዊ ደረጃ ት/ቤት አገልግሎት የሚገነባ ይሆናል፡፡ (ስለዚህ ኘሮጀክት፣ የእንግሊዝኛ እትም ብቻ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፒዲኤፍ መረጃ ይውሰዱ፡፡)

በአሁኑ ወቅት ቢለማ በባንሣ ውስጥ የአዋላጅ ትምህርት ኘሮግራም ለማልማትና የወሊድ ችግር ያለባቸው ሴቶች በአሁኑ ወቅት ችግር ሲገጥማቸው 180 ኪ.ሜ በአቧራ መንገድ ላይ በመጓዝ ስቃይ እንዳይደርስባቸው ለሴቶች የሚሆን የማዋለጃ ክሊኒክ ግንባታ ለማካሄድ ከአካባቢው መስተዳድር ጋር ሥምምነት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ለሁለቱም ኘሮጀክቶች የእርስዎን እርዳታ በደስታ የምንቀበለው ነው፡፡

እርዳታችሁ በሚከተለው ሂሣብ ቁጥር ተቀማጭ ሊሆን ይችላል፡-
የደች ፓስትባንክ ሂሣብ ቁጥር፡-5066864
ቪአይሲ ፒኤስቲቢኤንኤል21 አይቢኤኤን፡- ኤንኤል96ፒኤስቲቢ0005066842
በቢለማ ተቋም ሥም
ከተማ/ አገር፡ ቭላርዲንገን/ ዘ ኔዘርላንድስ
የቢለማ ተቋም በደች ደንብ(1956) አንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ መሠረት የተመሠረተ ተቋም ነው፡፡